የጨረታ ሰነዶች ማስታወቂያዎች1. ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የኤሌክትሪክ ኬብል ግዥ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አአቤግፕግግ 07/2011

የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕ/ጽ/ቤት የኤሌክትሪክ ኬብል ለሦስተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ በማውጣት የሀገር ውስጥ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ የተሠማሩ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አዲስ ሕንፃ ላይ 6ኛ ፎቅ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ክፍያና ሒሳብ ደ/የሥ/ሂደት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የኤሌክትሪክ ኬብል ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሠነዱን ሞልተው እስከሚመልሱበት ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት አስፈላጊውን ናሙና ወስደው በራሳቸው ወጪ በማስመርመር የተከፈለበትን ማስረጃ ከቴክኒክ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

ጨረታው ጥር 09 ቀን 2011 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ሕንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የግዥ እቅድ ዝግጅትና አፈጻጸም ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1

ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው አዲስ ሕንፃ

ስልክ ቁጥር +251118 78 79 45
የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

የጨረታ ሰነዶች አርካይቭ


©Addis Ababa Housing Development Project Office 2005-2018